Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

በድሬዳዋ  የመደመር  ትውልድ  መጻሕፍ  ትውውቅ ተካሄደ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 23፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር የመደመር  ትውልድ  መጻሕፍን የማስተዋወቅ  መርሃ ግብር ተካሂዷል፡፡

በመድረኩ የድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ከድር ጁሃር÷ “የመደመር ትውልድ” መፅሐፍ  ÷  አንድነትን፣  የዴሞክራሲ ሥርዓትን እና ተሥፋን በትውልድ ውስጥ  ለማዳበር  መሠረታዊ ሚና የሚጫወት መሆኑን  ተናገረዋል፡፡

መጻሕፉ በከፍተኛ ደረጃ  እንደሚሸጥም ከወዲሁ የተጠበቀ ሲሆን÷ መፅሐፉን የማስተዋወቅ ሥራ ለአንድ ሳምንት እንደሚቀጥልም ነው የተገለፀው፡፡

ከመፅሐፉ ሽያጭ የሚገኘው ገቢ  ዘመናዊ  ቤተ-መጻሕፍት  እና ሌሎች የልማት ፕሮጀክቶች የሚገነቡበት መሆኑንም ገለጸዋል።

በትውውቅ መድረኩ የድሬዳዋ ባለሐብቶች ፣ ነጋዴዎች ፣ የካቢኔ አባላት እና ሌሎች የኅብረተሰብ ክፍሎች በመርሐ-ግብሩ ላይ ተሳትፈዋል፡፡

#Ethiopia

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

Exit mobile version