Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

በጃዊ ወረዳ ጫካ ገብተው የነበሩ ቡድኖች እርቅ በመፈፀም  ወደ ቤታቸው ተመለሱ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 23፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በአዊ ብሄረሰብ አስተዳደር በጃዊ ወረዳ በተለያዩ ምክንያቶች ጫካ  ገብተው የነበሩ ቡድኖች እርቅ በመፈፀም  ወደ ቤታቸው  ተመለሱ።

የአዊ ብሄረሰብ አስተዳደር  ሰላምና ፀጥታ  መምሪያ  ኃላፊ ጌታቸው ቢሻው÷ በመንግስት የስራ ኃላፊዎች ላይ ቅሬታ  በማንሳት   ጫካ ገብተው  የነበሩ  ዜጎችን  በሀገር ሽማግሌዎች  አደራዳሪነት ወደ ቤታቸው መመለስ መቻሉን ገልፀዋል፡፡

የተጀመረው  የእርቅ ስምምነት  ወደ ኋላ እንዳይመለስ  የሀገር ሽማግሌዎችና አመራሩ አጠናክረው  የሚሰሩ  መሆኑን  የመምሪያው ኃላፊ ተናግረዋል።

በፕሮግራሙ  ላይ ያልተገኙት አባላት እንዲመጡ ለማድረግና ሰላም እንዲሰፍን  የበኩላቸውን ሚና እንደሚጫወቱም  በእርቀሰላሙ ላይ የተሳተፉ አባላት ተናግረዋል፡፡

በእለቱ 118 አባላት በፕሮግራሙ ላይ ተገኝተው በስምምነቱ ላይ የፈርሙ ሲሆን÷  የያዙትን የነፍስ ወከፍ መሣሪያ አስመዝግበው ሕጋዊ  ማድረግ  መቻላቸውን አሚኮ ዘግቧል፡፡

ሁሉም ዜጎች የሰላም  አስፈላጊነትን  በተገቢው መንገድ ተረድተው ለሰላም ዘብ እንዲቆሙ መልዕክት ተላልፏል፡፡

Exit mobile version