አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 24፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ካቢኔ መደበኛ ስብሰባውን በዛሬው ዕለት አካሂዷል፡፡
ካቢኔው በስብሰባው የክልሉን መልሶ ግንባታ አስመልክቶ የተዘጋጀ ዕቅድ ላይ መምከሩን የክልሉ ጊዜያዊ ርዕሰ መስተዳድር ጽ/ቤት መረጃ ያመላክታል፡፡
ከዚህ ባለፈም በክልሉ በቀጣይ ወራቶች በሚከናዎኑ ተግባራት ላይ አቅጣጫ ማስቀመጡ ነው የተገለጸው፡፡
የክልሉ ካቢኔ በመደበኛ ስብሰባው ወቅታዊ ሁኔታን በዝርዝር በመገምገም አቅጣጫ ማስቀመጡም ተጠቁሟል፡፡

