Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

ከንቲባ አዳነች የማልማት ጥያቄ አቅርበው ለፕሮጀክቶቻቸው መሬት ከተወሰነላቸው አልሚዎች ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ ፣ ሚያዝያ 25 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤ የማልማት ጥያቄ አቅርበው ፕሮጀክቶቻቸው ለከተማዋ ዕድገት ካላቸው የላቀ ፋይዳ እና ከሚፈቱት የህዝብ ችግር አኳያ መሬት በምደባ ከተወሰነላቸው ባለሀብቶች እና የዕምነት አባቶች ጋር ተወያዩ።

ከንቲባዋ እንዳስታወቁት 150 ሔክታር መሬት በምደባ ለመስጠት የተወሰነው ያቀረቧቸው ፕሮጀክቶች የከተማዋን ታላቅነት የሚመጥኑ፣ ለከተማው ነዋሪ ከሚፈጥሩት የስራ ዕድል፣ ለከተማዋ ዕድገት ከሚያበረክቱት የላቀ አስተዋጽዖ እንዲሁም ከሚያቃልሉት ማኅበራዊና ኢኮኖሚያዊ ችግር አኳያ በመሆኑ በታማኝነት እንደሚያለሙ መግባባት ላይ ተደርሷል።

በግልጽ አሰራር ባለሀብቶቹ ያቀረቡት ፕሮፖዛል ተፈትሾ በምደባ ለመስጠት የተወሰነው ከተማዋን የሚመጥኑ ግዙፍ እና ሁለገብ አገልግሎት የሚሰጡ ዘመናዊ ሞሎችና ሆቴሎች እንዲገነቡ፣ የከተማው ነዋሪ የስራ ዕድል እንዲፈጠርለትና የከተማዋ ገቢ እንዲጨምር ለማድረግ በመሆኑ ባለሀብቱ በከተማዋ ፍላጎት ልክ መዘጋጀትና ማልማት ይጠበቅበታል ተብሏል።

በውይይቱ ወቅት መሬት አልሚዎች በዚህ ልክ ግልጽነትና ፍትሃዊነት የነገሰበት አሰራር ተበጅቶ አልሚዎች ሆቴሎችና ሞሎች፣ የዕምነት ተቋማት ደግሞ የማምለኪያ ቦታ እንዲሰጣቸው መደረጉ ፍትሀዊነትና ዕኩልነት በተግባር ያሳየ በመሆኑ ለከተማ አስተዳደሩ ምስጋና አቅርበዋል።

በታማኘነት መሬቱን ለታለመለት ዓላማ በማዋል፣ መንግስት የከተማዋን ገጽታ የቀየሩ ታላቅ ፕሮክቶች በመገንባት እያደረገ ያለውን ስራ በተግባር በማገዝ የዜግነት ግዴታቸውን ለመወጣት እንደሚሰሩ ቃል መግባታቸውን አስታውቀዋል።

Exit mobile version