አዲስ አበባ፣ ግንቦት 1፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ይልቃል ከፋለ (ዶ/ር) ከዓለም አቀፉ ተራድዖ ድርጅት አስተባባሪዎች ጋር ተወያዩ።
ውይይቱ በክልሉ በጦርነት ምክንያት ጉዳት የደረሰባቸውን አካባቢዎች መልሶ ለማቋቋም እየተከናወኑ ባሉ ስራዎች ዙሪያ ትኩረት ያደረገ ነው ተብሏል።
በውይይቱ የተባበሩት መንግስታት የልማት ፕሮግራም፣ የአለም የምግብና እርሻ ድርጀት፣ የአለም ጤና ድርጅት፣ የሰብዓዊ ጉዳዮች ማስተባበሪያ ቢሮ እና የሌሎች ዓለም አቀፍ ተራድዖ ድርጅት አስተባባሪዎች ተሳትፈዋል፡፡
በአዲሱ ሙሉነህ