አዲስ አበባ፣ ግንቦት 4፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤ በታክስ ጎዳዮች ዙሪያ ከአምራቾችና አስመጪዎች ጋር ውይይት ማካሄዳቸውን አስታወቁ፡፡
በውይይታቸውም የተሠሩና ለውጥ ማምጣት የጀመሩ የአገልግሎት ማሻሻያ የሪፎርም ሥራዎች ተጠናክረው እንዲቀጥሉ መግባባት ላይ መደረሱን አስታውቀዋል።
በተጨማሪም ግብር መክፈል ውዴታ ብቻ ሳይሆን ግዴታ መሆኑን መግባባት ላይ መድረሳቸውን በማህበራዊ ትሥሥር ገጻቸው ገልጸዋል፡፡
የአዲስ አበባ ከንቲባ አዳነች አቤቤ ÷ ከግብር ሰብሳቢው ጋር ተቀራርቦ መሥራት ፣ ተገቢውን ክብር መሥጠት እንዲሁም ግብር በሚሰውሩና ግዴታቸውን በማይወጡ ነጋዴዎች ላይ አስተማሪ እርምጃ መውሰድ እንደሚገባም መግባባት ላይ መድረሳቸውን ጠቁመዋል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን

