አዲስ አበባ፣ ግንቦት 7፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤ የክረምት የበጎ ፍቃድ ቤት እድሳት መርሐ ግብርን አስጀምረዋል፡፡
መርሐ ግብሩ በልደታ ክፍለ ከተማ ወረዳ 1 በተለምዶ ቆርቆሮ ሰፈር ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ነው የተጀመረው፡፡
አካባቢው ቆርቆሮ በቆርቆሮ የተሰራ በመሆኑ እና የቤቱ አሰራር ለመኖሪያ ምቹ ባለመሆኑ ምክንያት በማህበረሰቡ ዘንድ የረጅም ጊዜ የመልካም አስተዳደር ጥያቄ ሆኖ መቆየቱ ተመላክቷል።
ይህን ችግር ለመቅረፍም አስተዳደሩና ክፍለ ከተማው በወሰዱት ቁርጠኝነት ዛሬ ከንቲባዋ በተገኙበት ቤቱን አፍርሶ በዘመናዊ መንገድ ለመገንባት የመሰረት ድንጋይ መቀመጡን ከክፍለ ከተማው ኮሙኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።
ከንቲባዋ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው እንዳሉት ፥ “ጠቅላይ ሚኒስትራችን ከሦስት ቀናት በፊት ያስጀመሩትን የክረምት በጎ ፈቃድ ስራ ተከትሎ እኛም ዛሬ 3 ሺህ 500 የሚሆኑ የመኖሪያ ቤት ዕድሳት አስጀምረናል”፡፡
ልበ-ቀና ባለሃብቶችንና ሕዝቡን በማስተባበር የበርካታ ነዋሪዎችን ችግር መቅረፍ የሚያስችል የቤት እድሳት መርሐ ግብር መሆኑንም ገልጸዋል፡፡
በዚህም በልደታ ክፍለ ከተማ በተለምዶ ቆርቆሮ ሰፈር ተብሎ በሚጠራው ከ18 ዓመታት በላይ በቆርቆሮ ቤት ውስጥ የሚኖሩ 134 አባወራዎችንና በአራዳ ክፍለ ከተማ ራስ መኮንን ድልድይ አካባቢ የሚኖሩ 15 አባወራዎችን መኖሪያ ቤት እድሳት ማስጀመራቸውን አንስተዋል፡፡
የከተማዋን ገጽታ የሚቀይር ታላላቅ ፕሮጀክቶችን ከመገንባት ጎን ለጎን በሰው ተኮር ስራዎች የሀገር ባለውለታዎችንና አቅመ ደካማ ነዋሪዎችን ከከተማዋ ዕድገት ፍትሐዊ ተጠቃሚ እንዲሆኑ በትጋት መስራታችንን እንቀጥላለንም ብለዋል::
#Ethiopia
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!