Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

በትራፊክ አደጋ የሚደርስን ሞት በ70 በመቶ ለመቀነስ እየተሰራ ነው-አለሙ ስሜ (ዶ/ር)

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 7፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በትራፊክ አደጋ የሚደርስን የሞት ምጣኔ በ70 በመቶ ለመቀነስ እየተሰራ መሆኑን የትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡

የትራንስፖርት እና ሎጂስቲክስ ሚኒስትር አለሙ ስሜ (ዶ/ር)  ከተባበሩት መንግስታት የመንገድ ደህንነት ተወካዮች ጋር በበይነ መረብ ተወያይተዋል፡፡

ውይይቱ ለ7ኛ ጊዜ በሚከበረው የ2023 የተባበሩት መንግስታት ዓለም አቀፍ የመንገድ ደህንነት ሳምንት ላይ ያተኮረ መሆኑ ተገልጿል፡፡

ሚኒስትሩ በዚህ ወቅት እንዳሉት÷የመንገድ ደህንነት እና የአረንጓዴ ትራንስፖርት ጉዳይ በኢትዮጵያ የትራንስፖርት እና ሎጂስቲክስ ሀገራዊ ፖሊሲዎች ትኩረት የተሰጣቸው አጀንዳዎች መሆናቸውን ገልፀዋል፡፡

በትራንስፖርት ዘርፉ የ10 ዓመት መሪ የልማት እቅድ ላይ በማካተት የመንገድ ደህንነት ችግሮችን በመፍታት የሚደርሰውን የሞት አደጋ በ70 በመቶ ለመቀነስ በትኩረት እየተሰራ መሆኑን አንስተዋል፡፡

የብዙሃን ትራንስፖርት ማስፋፋት፣ የትራንስፖርት ሴክተሩን ከካርቦን ልቀት ነፃ የማድረግ እና የሞተር አልባ ትራንስፖርትን ለማስፋፋት እየተሰሩ ባሉ ስራዎች ላይ ገለጻ ማድረጋቸውንም የሚኒስቴሩ መረጃ ያመላክታል፡፡

Exit mobile version