አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 15፣ 2012(ኤፍ ቢ ሲ)የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝን ለመከላከል ለሚደረገው እንቅስቃሴ የተለያዩ አካላት ድጋፍ ማድረጋቸውን ቀጥለዋል።
በዚህም በዛሬው ዕለት 4 ነጥብ 8 ሚሊዮን ብር የገንዘብ እና የአይነት ድጋፍ የተደረገ ሲሆን÷ በዚህ ድጋፍ 49 የተለያዩ ድርጅቶችና ባለሀብቶች መሳተፋቸውም ነው የተገለጸው።
የገንዘብ እና የአይነት ድጋፉን በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የመንግስት አገልግሎት ሰጪ ተቋማት አስተባባሪ ኢንጅነር እንዳወቅ አብቴ ተቀብለዋል፡፡
በዚሁ ወቅት ድርጅቶቹ እና ባለሀብቶቹ ላደረጉት የገንዘብ ፣ የአይነት ድጋፍ እና ነጻ የኪራይ ክፍያ ኢንጂነር እንዳወቅ በከተማ አስተዳደሩ ስም ምስጋናቸውን አቅርበዋል፡፡
ድጋፉን ካበረከቱት መካከል የተለያዩ ማህበራት፣ የገበያ ማዕከላት፣ ኢንዱስትሪዎች፣ ሞሎች እና ግለሰቦች መሳተፋቸውን ኢዜአ ዘግቧል ።

