Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

ባለፉት 10 ወራት ከ20 ሺህ በላይ ግብር ከፋዮች የኤሌክትሮኒክ የክፍያ ዘዴን ተጠቅመዋል -ሚኒስቴሩ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 9፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ባለፉት 10 ወራት ከ20 ሺህ በላይ ግብር ከፋዮች የኤሌክትሮኒክ የክፍያ ዘዴን በመጠቀም ከ61 ቢሊየን ብር በላይ መክፈላቸውን የገቢዎች ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡

በገቢዎች ሚኒስቴር የገቢ ሂሳቦች ዳይሬክቶሬት ገቢ ሂሳቦች ማጠቃለያ ቡድን አስተባባሪ ኤልሳቤጥ አሸናፊ እንደገለፁት÷ ግብራቸውን ከከፈሉ 20 ሺህ 772 ግብር ከፋዮች ውስጥ 8 ሺህ 56 ግብር ከፋዮች በዘንድሮ የበጀት ዓመት የተመዘገቡ ግብር ከፋዮች ናቸው፡፡

በዚህ የክፍያ ዘዴም ባለፉት 10 ወራት ውስጥ 61 ቢሊየን ብር በላይ ገቢ መሰብስሰብ መቻሉን ነው ያመላከቱት፡፡

ስርዓቱ ግብር ከፋዮች ከአላስፈላጊ የገንዘብና የጊዜ ብክነት ተላቀው በቀላሉ ግዴታቸውን እንዲወጡ ያስቻለ መሆኑንም ገልፀዋል፡፡

የኤሌክትሮኒክ መክፈያ ስርዓት ከተዘረጋበት ጊዜ ጀምሮ እስካሁን ከ22 ሺህ በላይ ግብር ከፋዮች በአዲሱ የክፍያ ዘዴ የከፈሉ ሲሆን 127 ቢሊየን ብር ባለይ ተሰብስቧል መባሉን ከገቢዎች ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

Exit mobile version