Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

ማንቼስተር ሲቲ የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ሻምፒዮን መሆኑን አረጋገጠ

አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 12 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ማንቼስተር ሲቲ የአንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ 2022/23 የውድድር አመት ሻምፒዮን መሆኑን አረጋግጧል፡፡

ውሃ ሰማያዊዎቹ ዛሬ አርሰናል በኖቲንግሃም ፎረስት መሽነፉን ተከትሎ ነው 3 ጨዋታዎች እየቀሩት የሊጉ ሻምፒዮን መሆን የቻለው፡፡

ለ3 ዋንጫ ሲፎካካሩ የነበሩት ዘ ሲትዝንስ ከሊጉ ዋንጫ በተጨማሪ በእንግሊዝ ኤፍ ኤ ካፕ እና በአውሮፓ ቻምፒንስ ሊግ ለፍፃሜ ደርሰዋል፡፡

ኬቨን ደ ብሩይነ ከሲቲ ጋር 5 ዋንጫዎችን በማንሳት በክለቡ ታሪክ ብዙ የፕሪሚየር ሊግ ዋንጫ ባለቤት መሆን የቻለ ተጫዋች ሆኗል፡፡

ከዚህ በፊት ሰርጂዮ አጉዌሮ፣ ዴቪድ ሲልቫ እና ቪንሰንት ኮምፓኒ ከማንቼሰተር ሲቲ ጋር 4 ጊዜ ፕሪሚር ሊጉን ዋንጫ ማንሳት የቻሉ ተጫዋቾች ናቸው፡፡

በሌላ በኩል አርሰናልን 1 ለ 0 ያሸነፈው ኖቲንግሃም ፎረስት በሊጉ መቆየቱን አረጋግጧል፡፡

Exit mobile version