አዲስ አበባ፣ ግንቦት 15፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በኢትዮጵያ የ ተ. መ. ድ. ዋና ተጠሪና የሰብአዊ ድጋፍ ዋና አስተባባሪ ዶ/ር ካትሪን ሶዚ የአገልግሎት ዘመናቸውን በማጠናቀቃቸው በኢፌዴሪ የአደጋ ሥጋት አመራር ኮሚሽን ሽኝት ተደረገላቸዋል፡፡
በሽኝት ፕሮግራሙ የኮሚሽኑ ኮሚሽነር አምባሳደር ዶ/ር ሽፈራው ተ/ ማርያም ሀላፊዋ በቆይታቸው ላሥመዘገቡት ብቁ አፈጻጸም ምሥጋና አቅርበዋል፡፡
ኃላፊዋም በተደረገላቸው ሽኝት ፕሮግራም አመስግነው በኢትዮጵያ የነበረኝ ቆይታ የማይረሳ ነው ብለዋል፡፡
ኢትዮጵያ በተለይ በግብርናው ዘርፍ በርካታ አስደማሚ ለውጦችን ማስመዝገቧንም ገልጸዋል።
ለውጡ በዚህ ፍጥነት ከቀጠለ ኢትዮጵያ ከዕርዳታ የምትላቀቅበት ጊዜ ሩቅ እንደማይሆን መስክረዋል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!