Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

ኮሚሽነር ለሊሴ ነሜ በኢትዮጵያ ከቱርክ አምባሳደር ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 16 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን ኮሚሽነር ለሊሴ ነሜ (ኢ/ር) በኢትዮጵያ ከቱርክ አምባሳደር ቤርክ ባራን ጋር ተወያይተዋል።

ውይይቱ የቱርክ ባለሀብቶች በኢትዮጵያ ተመራጭ ባደረጓቸው የኢንቨስትመንት እድልና አማራጮች ላይ ያተኮረ መሆኑ ተገልጿል።

ከዚህ ባለፈም የጋራ የኢትዮጵያን የኢንቨስትመንት ዘርፍ የማስተዋወቅ ስራ ላይ ያተኮረ መሆኑን የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን መረጃ ያመላክታል።

Exit mobile version