አዲስ አበባ፣ ግንቦት 18፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የደቡብ ክልል ከፍተኛ የሥራ ሃላፊዎች የውይይት መድረክ በሐዋሳ ከተማ እየተካሄደ ነው።
ውይይቱ “በጠንካራ ፓርቲ መሪነት ቅቡልነት ያለውን ሀገረ-መንግስት ግንባታ እውን እናደርጋለን” በሚል መሪ ቃል ነው እየተካሄደ የሚገኘው፡፡
የክልሉ ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ ቤት አደረጃጀት ዘርፍ ኃላፊ አቶ ይሁን አሰፋ እንደገለጹት÷ብልጽግና ፓርቲ በበርካታ ፈተናዎች መካከል ሆኖ ከፍተኛ ድሎችና ውጤቶችን እያስመዘገበ የመጣ ፓርቲ ነው።
ፓርቲውን በየጊዜው እያጋጠሙ ያሉ ፈተናዎችን መመከት የሚያስችሉ የአደረጃጀቶችና ተቋማትን አቅም በማጠናከር በኢትዮጵያ ቅቡልነት ያለው መንግስት ለመገንባት እየተሰራ መሆኑን ገልጸዋል።
ብልጽግና ፓርቲ የጀመራቸው የፓርቲው ፖሊሲዎች፣ ፕሮግራሞችና እቅዶች እንዲሳኩ አመራሩ፣ አባላትና ደጋፊዎች ጠንክረው እንዲሰሩ አሳስበዋል።
ነጻነትን በአግባቡ ከማስተዳደር አኳያ እያጋጠሙ ያሉ ተግዳሮቶች እየታረሙ እንዲሄዱ እየተሠራ መሆኑንም ጠቅሰዋል።
በኮንፈረንሱ ላይ የክልሉ ከፍተኛ አመራሮች የተሳተፉ መሆኑን የክልሉ ብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት መረጃ ያመላክታል፡፡