Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

ለ1 ሺህ 19 ሰዎች ምርመራ ተደርጎ 5 ሰዎች የኮሮናቫይረስ ተገኘባቸው

አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 17፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በኢትዮጵያ ባለፉት 24 ሰአታት ውስጥ በተደረገ ምርመራ ተጨማሪ 5 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ እንደተገኘባቸው የጤና ሚኒስትር ዶክተር ሊያ ታደሰ አስታወቁ።
በ24 ሰአታት ውስጥ ለ1 ሺህ 19 ሰዎች ሰዎች የኮሮና ቫይረስ ምርመራ መደረጉን የጤና ሚኒስትሯ ዶክተር ሊያ ታደሰ ገልፀዋል።
 
ሚኒስትሯ በተደረገው ምርመራም ተጨማሪ 5 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ እንደተገኘባቸው የገለፁ ሲሆን፥ ይህንን ተከትሎም በኢትዮጵያ የኮሮና ቫይረስ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር 122 ደርሷል ብለዋል።
 
ቫይረሱ ከተገኘባቸው ሰዎች ውስጥ አንዷ የ75 ዓመት እድሜ ያላቸው ሴት ኢትዮጵያዊት ሲሆኑ፥ ነዋሪነታቸው አዲስ አበባ፣ የጉዞ ታሪክ የሌላቸው እና በቫይረሱ ከተያዘ ሰው ጋር ንክኪ እንዳላቸው በመጣራት ላይ መሆኑን አስታውቀዋል።
 
ቀሪዎቹ አራቱ የ39፣ የ49፣ የ59 እና የ28 ዓመት እድሜ ያላቸው ቻይናውያን ሲሆኑ፥ የጉዞ ታሪክ የሌላቸው እና በቫይረሱ ከተያዘ ሰው ጋር ንክኪ ያላቸው መሆኑንም አስታውቀዋል።
 
ዶክተር ሊያ አክለውም ባለፉት 24 ሰዓታት 4 ተጨማሪ ሰዎች ከቫይረሱ ማገገማቸውን በመጥቀስ፥ ይህንን ተከትሎም በኢትዮጵያ ከቫይረሱ ያገገሙ ሰዎች ቁጥር 29 መድረሱን ገልፀዋል።
 
በአጠቃላይ በኢትዮጵያ የኮሮናቫይረስ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር 122 ሲሆን፥ ከእነዚህም ውስጥ 88 ሰዎች በለይቶ ህክምና ላይ፤ 29 ሰዎች ደግሞ ከቫይረሱ ማገገማቸው ይታወቃል።

ትኩስ መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት የቴሌግራም ገፃችንን ሰብስክራይብ ያድርጉ!
https://t.me/fanatelevision

Exit mobile version