Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

የሶማሌ ክልል ምክትል ርዕሠ-መስተዳድር የግብርና ሳይንስ አውደ ርዕይን ጎበኙ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 23፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ)የሶማሌ ክልል ምክትል ርዕሠ-መስተዳድር አቶ ኢብራሂም ዑስማን የግብርና ሳይንስ አውደ ርዕይን ጎበኙ።

ከዕርሳቸው ጋር የክልሉ አመራሮች በሳይንስ ሙዚየም የቀረቡ የግብርና ውጤቶችን፣ የግብርና ሳይንስ እንዲሁም ዘርፉ የደረሰበትን ደረጃ ተዘዋውረው ተመልክተዋል።

ከጉብኝቱ ጎን ለጎን በሳይንስ ሙዚየሙ የተዘጋጀውን የሶማሌ ክልል የግብርና አውደ ርዕይ ምክትል ርዕሠ-መስተዳድሩ ከፍተው አስጀምረዋል።

በክልል ደረጃ በተዘጋጀው የግብርና አውደ ርዕይ ላይ በክልሉ የተመረቱ አትክልትና ፍራፍሬ፣ የእንስሳት ተዋጽኦና የሰብል ምርቶች ለዕይታ መቅረባቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
Exit mobile version