Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

የኢትዮጵያ ሚቲዮሮሎጂ ኢንስቲትዩት ከቻይና ሚቲዮሮሎጂ አስተዳደር ጋር ተፈራረመ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 23፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ሚቲዮሮሎጂ ኢንስቲትዩት እና የቻይና ሚቲዮሮሎጂ አስተዳደር የጋራ የስራ ስምምነት ተፈራረሙ፡፡

ከ19ኛው የዓለም ሚቲዮሮሎጂ ድርጅት ኮንግረንስ ጎን ለጎን የኢትዮጵያ ሚቲዮሮሎጂ ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር አቶ ፈጠነ ተሾመ ከተለያዩ የተቋማት የስራ ኃላፊዎች ጋር በትብብር ለመስራት ውይይት እና ስምምነት አድርገዋል፡፡

ስምምነቱ የኢትዮጵያ ሚቲዮሮሎጂ ኢንስቲትዩትና የቻይና የሚቲዮሮሎጂካል አስተዳደር ልዑካን ቡድን በተገኙበት መፈረሙን የኢትዮጵያ ሚቲዮሮሎጂ ኢንስቲትዩት መረጃ ያመላክታል፡፡

ሁለቱም የሚቲዮሮሎጂ ተቋማት በጥናትና ምርምር ዙሪያ፣ በቴክኖሎጂና ዕውቀት ሽግግር፣ በልምምድ ልውውጥ እና በመሰረተ ልማት አውታሮች ዙሪያ በቅንጅት ለመስራት ተስማምተዋል ተብሏል፡፡

Exit mobile version