አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 17፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በአዲስ አበባ ከተማ በየካ ክፍለ ከተማ አምባሳደር መኖሪያ መንደር ኗሪዎች አቅመ ደካማ ለሆኑ ዜጎች ድጋፍ አደረጉ።
የመኖሪያ መንደሩ ኗሪዎች በአካቢያቸው ለሚገኙ 190 አባወራዎች ነው የምግብ ዘይት፣ ዱቄት፣ ማካሮኒ እና ሌሎች ለምግብነት የሚውሉ ግብአቶችን የለገሱት።
የድጋፍ አስተባባሪ እና የመኖሪያ መንደሩ ቦርድ ሊቀመንበር ዶክተር መሳፍንት አበበ ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት እንዳሉት፥ የኮሮና ቫይረስ ስርጭትን ለመግታት ዜጎች በቤታቸው እንዲቆዮ ይመከራል፤ በዚህ ወቅት የእለት ገቢያቸው ዝቅተኛ የሆኑ የሆኑ የህብረተሰብ ክፍሎች ችግር እንዳያጋጥማቸው ድጋፋ የተደረገ ነው።
በመኖሪያ መንደሩ የሚኖሩ 50 የሚደርሱ ቤተሰቦች ዛሬ ያደረጉት ድጋፍ የመጀመሪያ ዙር እንደሆነ የተናገሩት ዶክተር መሳፍንት፥ በቀጣይም አቅመ ደካማ ለሆኑ የአካባቢው ኗሪዎች ድጋፉ እንደሚቀጥልም ገልፀዋል።
አሁን ላይ የተደረገው ድጋፍ እስከ 130 ሺህ ግምት ያለው መሆኑንምበመግለፅ፥ መሰል ድጋፎችን በጋራ በማድረግ ዝቅተኛ ገቢ ያላቸውን ዜጎች በዚህ አስቸገሪ ወቅት ልንደርስላቸው ይገባል ብለዋል”
ድጋፍ የተደረገላቸው የአካባቢው ኗሪዎች ለበጎ አድራጊዎቹ ምስጋና አቅርበዋል፡፡
በአወል አበራ
የዜና ሰዓት ሳይጠብቁ የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬትን ትኩስ እና ሰበር ዜናዎችን በፍጥነት በአጭር የፅሁፍ መልዕክት መልክ በስልክዎ ላይ እንዲደርስዎ ወደ 8111 OK ብለው ይላኩ።

