Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል የሐላላ ኬላ ሪዞርትን ከጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት ተረከበ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 24፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ)የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግስት የሐላላ ኬላ ሪዞርትን ከጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት በይፋ ተረክቧል፡፡

የክልሉ መንግስት የ’ገበታ ለ ሀገር’ ፕሮጄክት አካል የሆነው እና በኮይሻ ፕሮጄክት ክላስተር ሥር የለማውን የሐላላ ኬላ ሪዞርት ነው ከጽህፈት ቤቱ የተረከበው፡፡

ሪዞርቱን ‘ሐላላ ኬላ ሪዞርት’ በሚል ስያሜ ለማስተዳደር የክልሉ መንግሥት ከፓራዳይዝ ሎጅዎች፤ ሪዞርቶች እና ሆቴሎች ማኔጅመንት ኃ/የተ/የግ/ማኅበር ጋር ስምምነት ማድረጉን ከጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

Exit mobile version