Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

በፕሪሚየር ሊጉ መቻል ወልቂጤ ከተማን አሸነፈ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 4፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በ28ኛ ሳምንት የቤትኪንግ ኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ መቻል ወልቂጤ ከተማን 2 ለ 0 በሆነ ውጤት አሸንፏል፡፡

ዛሬ 9 ሰዓት ላይ በአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ ምንይሉ ወንድሙ እና ግሩም ሀጎስ ለመቻል ግቦችን አስቆጥረዋል፡፡

በሌለ በኩል÷ከምሽቱ12 ሰዓት ላይ ፋሲል ከነማ ከኢትዮጵያ መድን ጋር ጨዋታቸውን እንደሚያደርጉ የቤትኪንግ ኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ መረጃ ያመላክታል፡፡

Exit mobile version