Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

10 የአውሮፓ ሀገራት ለዩክሬን የ116 ሚሊየን ዶላር የመሳሪያ ድጋፍ ይፋ አደረጉ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 7፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) 10 የአውሮፓ ሀገራት ለዩክሬን የ116 ሚሊየን ዶላር ድጋፍ ይፋ አድርገዋል።

ድጋፉ ለኪየቭ የአየር ኃይል ለማጠናከር የሚውል መሆኑም ተገልጿል።

ዩክሬን የሚደርሳት የዓይነት ድጋፍ በፈረንጆቹ ነሐሤ 2022 ላይ “ለዩክሬን ዓለም አቀፍ ፈንድ” በሚል በዴንማርኳ ኮፐንሀገን በተካሄደው ኮንፈረንስ ላይ በተቋቋመውና በብሪታንያ በሚመራው ጥምር ኃይል በኩል እንደተከፈለም ሺንዋ ዘግቧል፡፡

በብሪታኒያ የሚመራው ጥምር ኃይል ÷ የተገኘውን ገንዘብ ብሪታኒያን ጨምሮ ከዴንማርክ ፣ ስዊድን ፣ ኖርዌይ ፣ ፊንላንድ ፣ አይስላንድ ፣ ኔዘርላንድን ፣ ኢስቶኒያ ፣ ላቲቪያ እና ሉቴንያን ያካተተ ነው።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
Exit mobile version