አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 7 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በግሪክ ፍልሰተኞችን አሳፍራ ስትጓዝ የነበረች ጀልባ በመስጠሟ 59 ሰዎች መሞታቸው ተሰምቷል፡፡
የግሪክ የባህር ጠረፍ ጠባቂዎች አንዳስታወቁት÷ ጀልባዋ ፔሎፖኔዝ በተባለው የባህር ዳርቻ ከፔሎስ ከተማ በስተደቡብ ምዕራብ አቅጣጫ በሚገኘው ባህር ውስጥ ነው የሰጠመችው።
እስካሁን ከጀልባዋ 100 ሰዎችን ማዳን እንደተቻለም ነው የተነገረው።
በጀልባዋ ውስጥ ያሉት ተሳፋሪዎች ትክክለኛ ቁጥር አለመታወቁ የተገለፀ ሲሆን ጀልባዋ ምስራቃዊ ሊቢያ ወደ ግሪክ ባህር ስትቀዝፍ እንደነበር ተገምቷል፡፡
ባለፈው እሁድ የአሜሪካ ባንዲራ በተሰቀለበት ጀልባ ላይ የነበሩ 90 ስደተኞች በግሪክ የባህር ጠረፍ አካባቢ የአደጋ ጥሪ ማድረጋቸውን ተከትሎ በአካባቢው የነበሩ የነፍስ አድን ሰራተኞች መትረፍ ማቻላቸውን አልጀዚራ ዘግቧል፡፡