Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

የ2023/2024 የእንግሊዝ ፕሪሚየርሊግ የውድድር መርሐ ግብር ይፋ ሆነ

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 8 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የ2023/2024 የእንግሊዝ ፕሪሚየርሊግ የውድድር መርሐ ግብር ይፋ ሆነ፡፡

መርሐ ግብሩ እንዳመላከተው የፕሪሚየር ሊጉ የውድድር ሳምንት በፈረንጆቹ ነሐሴ 11 ቀን 2023 ይጀመራል፡፡

በመክፈቻው ዕለትም የእንግሊዝ እና የአውሮፓ ሻምፒዮኑ ማንቸስተር ሲቲ ከአዲስ አዳጊው በርንሌይ ጋር ጨዋታቸውን ያደርጋሉ፡፡

እንዲሁም በዚሁ የመጀመሪያ ሳምንት የጨዋታ መርሐ ግብር ላይ ቼልሲ ሊቨርፑልን ይገጥማል፡፡

በተጨማሪም አርሰናል ኖቲንግሃም ፎረስትን እንዲሁም ማንቼስተር ዩናይትድ ወልቭስን በመጀመሪያው ሳምንት የሚጫወቱ ይሆናል፡፡

Exit mobile version