አዲስ አበባ፣ ሰኔ 8፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በሀገራዊ የምክክር ኮሚሽኑ አጀንዳ ማሰባሰብና ተሳታፊዎች ልየታ የፖለቲካ ፓርቲዎች በተሳታፊነት ብቻ ሳይሆን በባለቤትነትም እንዲካተቱ እየተደረገ መሆኑን የሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ገለጸ፡፡
ተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲዎች ባለው ሂደት ውስጥ የምክክሩ ተሳታፊ ብቻ ሳይሆን ባለቤት የሚሆኑበትም እድል መፈጠሩን የኮሚሽኑ ምክትል ሰብሳቢ ወ/ሮ ሂሩት ገብረስላሴ ተናግረዋል፡፡
ከፓርቲዎቹ የጋራ ምክር ቤት ተዋካዮችን በአማካሪነት ማካተት አንደተቻለም ምክትል ሰብሳቢዋ ከፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ጋር ባደረጉት ቆይታ ተናግረዋል፡፡
የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት ሰብሳቢ መብራቱ አለሙ (ዶ/ር) በበኩላቸው÷በአጀንዳ አሰባሰቡና ተሳታፊ ልየታው የጋራ ሂደት መጀመሩን አረጋግጠዋል፡፡
ባለፉት ጊዜያት ከነበሩት ሂደቶች በተጨማሪ አሁን ለተጀመረው የአጀንዳ ማሰሰባሰብና ተሳታፊዎች ልየታም የጋራ አቅጣጫ መቀመጡን አንስተዋል፡፡
በኮሚሽኑ አማካሪ ቡድን በአማካሪነቱ ሚና የጋራ ምክር ቤቱ ተወካዮች መሳተፋቸውንም ነው ሰብሳቢው የተናገሩት፡፡
በአሸናፊ ሽብሩ
#Ethiopia
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!