Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

የመንጋጋ መገጣጠሚያ ህመም ምንድን ነው?

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 10፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የመንጋጋ መገጣጠሚያ ህመም በአብዛኛው ሴቶች ላይ እንዲሁም ወጣትና አረጋውያን ላይ ይከሰታል።

ከምክንያቶቹ መካከል÷ በአብዛኛው በፊት ላይ በሚፈጸም ድብደባ፣ አገጭ ላይ ምት ሲኖር ወይም ሌላ ጉዳት ሲኖር የሚሉት ይተቀሳሉ፡፡

እንደዚህ ዓይነት ህመሞች÷ የመገጣጠሚያ ጉዳት፣ በጡንቻ መቆጣት እንዲሁም በአጥንት ላይ  የሚደርስን ጉዳት ተከትሎ  ይከሰታሉ፡፡

እንዲሁም የጥርስ ሙሌት ከፍ ተደርጎ ሲሞላ፣ በትክክል ያልተሰራ ሰው ሠራሽ ጥርስ፣ የጥርስ መፋጨት፣ ጭንቀትና ድባቴ  ለመንጋጋ መገጣጠሚያ በምክንያትነት ይጠቀሳሉ፡፡

የመንጋጋ መገጣጠሚያ ህመም ምልክቶች መገጣጠሚያው ላይ እንዲሁም ከመገጣጠሚያው ውጭ ሊታዩ ይችላሉ።

ከምልክቶቹ መካከል÷ አፍን እንደወትሮ ለመክፈት መቸገር፣ የመገጣጠሚያ ህመም መሰማት፣ ምግብ ሲታኘክ ድምፅ መሰማት፣ አፍ ተከፍቶ አልዘጋም ማለት፣ የመገጣጠሚያ አካባቢ እብጠት፣ የጆሮ መጮህ  እና ራስ ምታት ይጠቀሳሉ፡፡

በተጨማሪም የአገጭ መገጣጠሚያ  ህመም፣ የአንገት እንዲሁም የጭንቅላት ጡንቻ ህመም፣ እንቅልፍ የመተኛት ችግር፣ ጥርስን ማፋጨት የመንጋጋ ህመም  ምልክቶች ናቸው፡፡

ሕክምናው እንደ ህመሙ ደረጃ የሚወሰን ሲሆን÷ ከህመም ማስታገሻ፣ ጥርስ ላይ የሚደረግ መሸፈኛ፣ የመገጣጠሚያ እጥበት እና በቀዶ ጥገና ሕክምናው ይሰጣል፡፡

Exit mobile version