Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

የቻይና ባለሃብቶች በመቀሌ ኢንዱስትሪ ፓርክ መዋዕለ ንዋያቸውን እንዲያፈሱ ጥሪ ቀረበ

አዲስ አበባ፣ሰኔ 12፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በኢትዮጵያ የቻይና አምባሳደር ዣኦ ዢዩዋን የተመራ ልዑክ የመቀሌ ኢንዱስትሪ ፓርክን ወቅታዊ እንቅስቃሴ ጎብኝቷል፡፡

የልዑካን ቡድኑ አባላት በጉብኝቱ ወቅት÷ ከመቀሌ ኢንዱስትሪ ፓርክ ስራ አስኪያጅ አቶ ፊሊሞን ተረፈ እና የፓርኩ የስራ ኃላፊዎች ጋር በተለያዩ ጉዳዮች ላይ መክረዋል፡፡

የቻይናው ኮንስትራክሽን ኩባንያ (ሲ ሲ ሲ ሲ ) በፓርኩ እያከናወናቸው የሚገኙ ፕሮጀክቶች የተጎበኙ ሲሆን÷ በቀጣይ ፕሮጀክቱ በፓርኩ ስለሚያከናውናቸው ስራዎችም ውይይት ተደርጓል።

የመቀሌ ኢንዱስትሪ ፓርክ ወደ ስራ እየገባ መሆኑን ተከትሎም የቻይና ባለሃብቶች በፓርኩ በተለያዩ ዘርፎች በኢንቨስትመንት እንዲሰማሩ ጥሪ መቅረቡን የኮርፖሬሽኑ መረጃ ያመላክታል፡፡

የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን የመቀሌ ኢንዱስትሪ ፓርክን ወደ ስራ ለመመለስ በአመራሮች የታገዘ ቡድን በማቋቋም አስፈላጊውን ቅድመ ዝግጅት ማጠናቀቁ ተጠቁሟል፡፡

Exit mobile version