Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

በብሪታኒያ የንግድ ሚኒስቴር የተመራ ልዑክ የቦሌ ለሚ ኢንዱስትሪ ፓርክን ጎበኘ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 12፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በብሪታኒያ የንግድ ሚኒስቴር ኒጌል ሀድልስቶን የተመራ ከፍተኛ የልዑካን ቡድን በቦሌ ለሚ ኢንዱስትሪ ፓርክ ይፋዊ የሥራ ጉብኝት አደረገ፡፡

ልዑኩ በቀጣይ የብሪታኒያ ባለሐብቶች በኢትዮጵያ ኢንዱስትሪ ፓርኮች ውስጥ መዋዕለ ንዋያቸውን ማፍሰስ በሚችሉበት ሁኔታ ላይ ይመክራል መባሉን የኮርፖሬሽኑ መረጃ ያመላክታል፡፡

ከውይይቱ በኋላም የብሪታኒያ ባለሐብቶች በኢንቨስትመንት በሚሰማሩበት ሁኔታ እና ሌሎች ጉዳዮች ከኮርፖሬሽኑ ጋር በቀጣይ መሥራት በሚችሉባቸው ጉዳዮች ላይ ከሥምምነት ላይ ይደርሳሉ ተብሎ ይጠበቃል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
Exit mobile version