Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

የወላይታ ዞን ሕዝበ ውሳኔ ምርጫ ድምጽ አሰጣጥ ሒደት ተጠናቀቀ

አዲስ አበባ፣ሰኔ 12፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በወላይታ ዞን ሲካሄድ የዋለው ሁለተኛው ዙር የሕዝበ ውሳኔ ምርጫ ድምጽ አሰጣጥ ሒድት ተጠናቅቋል፡፡

አሁን ላይም በየምርጫ ጣቢያዎቹ የድምጽ ቆጠራ እየተከናወነ  እንደሚገኝ ተገልጿል፡፡

በነገው ዕለት ማለዳም የቆጠራው ውጤት ለሕዝቡ ይፋ ይደረጋል ተብሎ ይጠበቃል ።

በየምርጫ ጣቢያዎቹ የሕዝብ ፍሰት በመኖሩ  የድምጽ አሰጣጥ ሒደቱ እስከ ምሽቱ አንድ ሰዓት ተራዝሞ መጠናቀቁ ተመላክቷል፡፡

የብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ሰብሳቢ ብርቱካን ሚደቅሳ በሰጡት መግለጫ÷በወላይታ ዞን ዛሬ የተካሄደው ህዝበ ውሳኔ ድምጽ አሰጣጥ ሒደት 1 ሰዓት ከ20 ደቂቃ ላይ በሁሉም ጣቢያዎች ተጠቅቋል ብለዋል፡፡

በምርጫ ሒደቱ ሁለት የሀገር ውስጥ ተቋማት እውቅና ተሰጥቷቸው 168 ታዛቢዎች አሰማርተው እንደነበር አንስተዋል፡፡

የሰብዓዊ መብት ኮሚሽንም ሰባት የሰብዓዊ መብት ተከታታዮችን በተለያዩ የምርጫ ጣቢያዎች ማሰማራቱን ነው የገለጹት፡፡

በብዙ ጣቢያዎች ላይ ብዙ መራጮች በሚኖሩበት አካባቢ ለ6 ወራት መኖራቸውን የማያሳይ መታወቂያ ይዘው መገኘታቸውን ሰብሳቢዋጠቁዋል፡፡

ችግሩን ለመፍታትም ቦርዱ የማጣራት ስራ በማከናወን እና መራጮች ምስክር እንዲያቀርቡ በማድረግ ድምጽ መስጠታቸውን አስረድተዋል፡፡

Exit mobile version