አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 20፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የፈረንሣይ የጣለችው የእንቅስቃሴ ገደብ በአንድ ወር ውስጥ 62 ሺህ ሰዎችን ህይወት ማዳኑን የሀገሪቱ ጠቅላይ ሚኒስትር ገለጹ።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ ኤድዋርድ ፊሊፕ ÷ ሀገሪቱ የወሰደችው ጠንካራ የቁጥጥር እርምጃዎች በአንድ ወር ጊዜ ውስጥ የ62 ሺህ ሰዎችን ህይወት መታደጉን ገልጸዋል።
የፈረንሳይ መንግስት በአሁኑ ወቅት በአውሮፓውያኑ አቆጣጠር ከግንቦት11 ጀምሮ የጣለቻቸውን የእንቅስቃሴ ገደቦች ቀስ በቀስ ለማላላት ማቀዱን ተናግረዋል፡፡
ነገር ግን በወረርሽኙ በከፍተኛ ደረጃ በተጠቁ ክልሎች አሁንም በጥብቅ ህጎች ስር ይቆያሉ ብለዋል።
በዚህም ከግንቦት 11 ጀምሮ መዋእለ-ሕፃናት እና የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ቀስ በቀስ የሚከፈቱ ሲሆን ከሳምንት በኋላ የመካከለኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ይከተላሉም ነው ያሉት ፡፡
ሱቆች እና ገበያዎች እንደገና እንዲከፈቱ የተፈቀደላቸው ሲሆን ውሳኔው ቡና ቤቶች እና ምግብ ቤቶችን አይመለክትም ተብሏል ፡፡
ከዚያም ባለፈ ከመዋለ ህጻናት በስተቀር በሁሉም ትምህርት ቤቶች ፣ቸርቻሪ ነጋዴዎችና ደንበኞች እንዲሁም የሕዝብ የትራንስፖርት አገልግሎት ላይ የኮሮና ተሐዋሲ ስርጭትን ለመግታት ጭምብል ማድረግ ግዴታ ነው ተብሏል።
ነገር ግን ዕቅዱ ተግባራዊ የሚሆነው በሕግ አውጭዎች ድምጽ ከተሰጠበት በኋላ መሆኑንም ጠቁመዋል ፡፡
በፈረንሣይ እስካሁን 165 ሺህ 842 ዜጎች በኮሮና ቫይረስ የተያዙ ሲሆን 23 ሺህ የሚሆኑት ደግሞ ህይወታቸውን አጥተዋል፡፡
ምንጭ፡- ቢ.ቢ.ሲ
ትኩስ መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት የቴሌግራም ገፃችንን ሰብስክራይብ ያድርጉ!

