አዲስ አበባ፣ ሰኔ 14፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያ የዲጂታል ፐብሊክ ጉድስ አሊያንስ አባል ሆነች፡፡
በትብብሩ ኢትዮጵያ በመካተቷ የዲጂታል 2025 ስትራቴጂ እና ሀገር በቀል ኢኮኖሚን ለማሳደግ በር ከፋች መሆኑን የኢንፎርሜሽን መረብ ደኅንነት አስተዳደር ዋና ዳይሬክተር ሰለሞን ሶካ ገልጸዋል፡፡
በተጨማሪም ከሌሎች አባል ሀገራት ጋር ልምድ ልውውጥ ለማድረግ ምቹ ሁኔታ እንደሚፈጥር መናገራቸውን የአስተዳደሩ መረጃ ያመላክታል፡፡
የብሔራዊ መታወቂያ ፕሮጀክት ዋና ዳይሬክተር ዮዳሄ አርዓያስላሴ ÷ ኢትዮጵያ የትብብሩ አባል ሀገር በመሆኗ ሀገር አቀፍ የዲጂታል መሰረተ ልማት ለመገንባት እና ወጪ ለመቀነስ ትልቅ ፋይዳ አለው ብለዋል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!