Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

በፌዴራሊዝም፣ በመንግስታት ግንኙነትና የሰላም ግንባታ ላይ ውይይት ተካሄደ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 17፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በፌዴራሊዝም ፣ በመንግስታት ግንኙነት እና የሰላም ግንባታ በኢትዮጵያ በሚል ውይይት ተካሄደ፡፡

መድረኩን የሰላም ሚኒስቴር ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የፌዴራሊዝም ጥናት ማዕከል ጋር በመተባበር አዘጋጅቶታል፡፡

በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የፌዴራሊዝምና አስተዳደር ጥናት ማዕከል ኃላፊ ከተማ ዋቅጅራ (ዶ/ር)÷የመድረኩ ዓላማ በፌዴራሊዝም፣ በመንግስታት ግንኙነትና በሰላም ግንባታ ዙሪያ ያለውን ግንዛቤ እንዲያድግ ለማድረግና ለፖሊሲ ግብዓት የሚሆኑ ሃሳቦችን ለመሰብሰብ ነው ብለዋል፡፡

በመድረኩ የፌዴራሊዝምና ሕገመንግስታዊ ሥር-ዓት ለሰላም ግንባታ ያለው ሚና፣ ኃይማኖቶች ለሰላም ያላቸው ሚና፣ የክልሎች ግንኙነት ለሰላም ግንባታና የተፈጥሮ ኃብት አስተዳደር ሰላም ያለው ተጽዕኖ ላይ ምክክር ተድርጓል፡፡

የሰላም ሚኒስትር አማካሪ አምባሳደር እሸቱ ደሴ ÷ የፌዴራል ስርዓቱ የማንነት ጥያቄዎችን ለመመለስ የሚያስችል ነው ብለዋል፡፡

ክልሎች የሚከሰቱ ችግሮችን በውይይት በመፍታት በጋራ የሚያድጉበትን መንገድ መፈለግ እንደሚኖርባቸው መገለጹን የሰላም ሚኒስቴር መረጃ ያመላክታል፡፡

Exit mobile version