አዲስ አበባ፣ ሰኔ 19፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በኦሮሚያ ከልል ምዕራብ ሸዋ ዞን አምቦ ከተማ ተልተሌ በሚባለው ቦታ በደረሰ የትራፊክ አደጋ የ10 ሰዎች ሕይወት አለፈ፡፡
በአምስት ሰዎች ላይ ደግሞ ከባድ የአካል ጉዳት መድረሱ ተገልጿል፡፡
አደጋው የደረሰው ዛሬ 3፡00 ላይ ሲሆን ÷ ከአምቦ ወደ ጉደር ሰዎችን አሳፍሮ በመጓዝ ላይ የነበረ አነስተኛ የሕዝብ ተሸከርካሪ ከሌላ የደረቅ ጭነት ተሸከርካሪ ጋር በመጋጨታቸው ነው፡፡