አዲስ አበባ፣ ሰኔ 19፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የሲዳማ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ደስታ ሌዳሞ በምስራቅ ሲዳማ ዞን በንሳ ወረዳ ዳዬ ከተማ የተገነቡ ሶስት ትምህርት ቤቶች መርቀው ከፍተዋል።
ርዕሰ መስተዳድሩ በምረቃ ስነ ስርዓቱ ወቅት እንደገለፁት÷መንግስት በክልሉ ዘርፈ ብዙ የልማት ስራዎችን እያከናወነ እንደሚገኝ ገልፀዋል፡፡
በክልሉ በትምህርት ስርዓቱ ላይ ያጋጠመውን ስብራት ለመጠገን የክልሉ መንግስት ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ መሆኑንም አንስተዋል፡፡
የክልሉ የትምህርት ቢሮ ሃላፊ አቶ በየነ በራሳ በበኩላቸው÷ በክልሉ የትምህርት ጥራትን ለማረጋገጥ እና ትውልዱን በእውቀት ጎዳና ለማነፅ በትኩረት እየተሰራ መሆኑን አብራርተዋል፡፡
ሁለቱ ቅድመ መደበኛ ትምህርት ቤቶች በበንሳ ወረዳ በአሎ እና በቦንቤ ቀበሌ በባለሃብት ታምሩ ታደሰ እና አሰፋ ዱካሞ መገንባታቸው ተጠቁሟል፡፡
አንዱ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ደግሞ በዳዬ ከተማ በክልሉ መንግስት የተገነባ መሆኑን የክልሉ የክልሉ ፕሬስ ሴክሬታሪያት መረጃ ያመላክታል፡፡