Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

በ2014 በጀት ዓመት ከ15 ቢሊየን ብር በላይ ውዝፍ ተሰብሳቢ ሒሳብ ተገኘ

 

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 20፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በተለያዩ ተቋማት ከ15 ቢሊየን ብር በላይ ውዝፍ ተሰብሳቢ ሒሳብ መገኘቱን የፌደራል ዋና ኦዲተር መስሪያ ቤት የ2014 በጀት ዓመት ሪፖርት አመላከተ።

በወቅቱ ያልተወራረደ ውዝፍ ተሰብሳቢ ሒሳብን በተመለከተ ኦዲት በተደረጉ 131 መስሪያ ቤቶች በጠቅላላው ከ15 ቢሊየን 125 ሚሊየን ብር በላይ ብር በወቅቱ ያልተወራረደና ያልተሰበሰበ ሒሳብ መኖሩ በኦዲት መረጋገጡን ዋና ኦዲር መሰረት ዳምጤ ገልጸዋል፡፡

ጤና ሚኒስቴር፣ የውሃ፣ መስኖ፣ ቆላማ አካባቢና አካባቢ ልማት ሚኒስቴር፣ የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን፣ ባህልና ስፖርት ሚኒስቴር፣ የአደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን እና ትምህርት ሚኒስቴር በወቅቱ ያልተወራረደ ውዝፍ ተሰብሳቢ ሒሳብ ከተገኘባቸው ተቋማት ተጠቃሽ መሆናቸው ተጠቁሟል፡፡

ተሰብሳቢ ሒሳቦቹ ከዓመት ወደ ዓመት በሒሳብ መግለጫዎቹ ላይ የሚታዩ ከሆነ ታአማኒነትን ከማሳጣታቸውም በላይ የመንግስትና የሕዝብ ኃብት ለብክነት እንደሚያጋልጡ ተነስቷል፡፡

ስለሆነም ተቋማቱ በደንብና መመሪያ መሰረት እንዲያወራርዱ እና መሰብሰብ የማይችሉትን ደግሞ አጣርተው እርምጃ እንዲወስዱ መገለጹን የሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት መረጃ ያመላክታል፡፡

Exit mobile version