Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

ርዕሰ መስተዳድር ኦርዲን በድሪ የአረፋ በዓልን ምክንያት በማድረግ ማዕድ አጋሩ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 20፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የሀረሪ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ኦርዲን በድሪ የአረፋ በዓልን ምክንያት በማድረግ ለአረጋውያንና ለአካል ጉዳተኞች ማዕድ አጋርተዋል፡፡

አቶ ኦርዲን በድሪ የአረፋ በዓልን ምክንያት በማድረግ በሀረር ከተማ በሚገኘው አብርሃ ባህታ የአረጋውያንና አካል ጉዳተኞች ተሃድሶ ድርጅት በመገኘት ነው ማእድ ያጋሩት፡፡

ድርጅቱ አረጋውያን እና አካል ጉዳተኞች ተገቢውን እንክብካቤ የሚያገኙበት ተቋም እንዲሆን በክልሉ መንግስት ሲሰራ መቆየቱን ርዕሰ መስተዳድሩ ገልጸዋል፡፡

በማዕከሉ ለሚገኙ አረጋውያንና አካል ጉዳተኞች እየተደረገ የሚገኘው ድጋፍ ተጠናክሮ ይቀጥላልም ነው ያሉት አቶ ኦርዲን በድሪ።

አብርሃ ባህታ የአረጋውያንና አካል ጉዳተኞች ተሃድሶ ድርጅት በአሁኑ ወቅት 150 አረጋውያን እና አካል ጉዳተኞች እየተንከባከበ እንደሚገኝ ከክልሉ ኮሙኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

Exit mobile version