Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

ከንቲባ አዳነች በ90 ቀናት በሚከናወኑ ስራዎች ላይ ውይይት አካሄዱ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 20፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ለቀዳማይ ልጅነት ንቅናቄ ትግበራ ልዩ ትኩረት በመስጠት በ90 ቀናት የሚሰሩ ሌሎች ስራዎችን በተመለከተ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር መወያየታቸውን የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤ ተናገሩ፡፡

“ሕጻናት የነገ ተስፋ ለአዲስ አበባ” በሚል መሪ ሐሳብ ለተጀመረው የቀዳማይ ልጅነት ንቅናቄ ትግበራ ልዩ ትኩረት ሰጥተን በ90 ቀናት በሚከናወኑ ስራዎች ላይ በየደረጃው ከሚገኙ አመራሮች እና ባለድርሻ ተቋማት ኃላፊዎች ጋር መወያየታቸውን ከንቲባዋ በማኅበራዊ ትስስር ገፃቸው ገልጸዋል፡፡

ከተማችንን ሕፃናት ቦርቀው፣ በአካልና በአዕምሮ ጎልብተው የሚያድጉባት ምርጥ የአፍሪካ መዲና በማድረግ ጠንካራ ትውልድ መገንባታችንን እንቀጥላለን ብለዋል፡፡

Exit mobile version