አዲስ አበባ፣ ሰኔ 20፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የአዲስ አበባ እና የድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር ከንቲባዎች ለኢድ አል-አደሃ (አረፋ) በዓል የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላለፉ፡፡
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ በመልዕክታቸው÷ ለመላው የእስልምና እምነት ተከታዮች እንኳን ለ 1444ኛ የኢድ አል-አደሃ (አረፋ) በዓል በሰላም አደረሳችሁ ብለዋል፡፡
በዓሉ የሰላም፣ የፍቅር እንዲሆን፤ ለሀገራችን ሰላም መጎልበት ዱዓ የምታደርጉበት እንዲሁም በእስልምና አስተምህሮ መሰረት ያለው ለሌለው አካፍሎ ሁሉም ወገናችን በደስታ የሚውልበት እንዲሆን እመኛለሁ ብለዋል በመልዕክታቸው፡፡
የድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ከድር ጁሃር ÷ታላቁ የአረፋ በዓል የሰው ልጅ ለፈጣሪ እና ለእምነቱ ሲል ከባድ የሆኑ መከራዎችን ለመቀበል ያለውን ፈቃደኛነት በማስታወስ፤ በአንድነትና በፍቅር የሚከበር ፤መስዋዕትነት የሚዘከርበት ልዩ ቀን ነው ብለዋል፡፡