አዲስ አበባ፣ ሰኔ 21፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) 1 ሺህ 444ኛው የዒድ አል አድሃ (አረፋ) በዓል በድሬዳዋ ከተማ ተከብሯል፡፡
በዓሉ በርካታ የእስልምና እምነት ተከታዮች በተገኙበት በሰላት እና ተክቢራን እንዲሁም በተለያዩ ሃይማኖታዊ ስነ ስርዓቶች ተከብሯል፡፡
በአከባበር ስነ-ስርዓቱ የድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ከድር ጁሃር እና የድሬዳዋ እስልምና ጉዳዮች ምክር ቤት አመራሮች ተሳትፈዋል።