Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

የጃፓን ባለሃብቶች በኢትዮጵያ መዋዕለ ንዋያቸውን ለማፍሰስ ፍላጎት እንዳላቸው ገለጹ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 21፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በጃፓን የኢፌዴሪ ኤምባሲ በ”ኢትዮዮጵያ በኢንቨስትመንት ዘርፍ ለመሰማራት ጊዜው አሁን ነው” በሚል መሪ ሃሳብ የኢንቨስትመንት ሴሚናር አካሂዷል፡፡

በመርሐ ግብሩ የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር በለጠ ሞላ (ዶ/ር)፣ በጃፓን የኢትዮጵያ አምባሳደር ዳባ ደበሌ እና ከ100 በላይ የጃፓን ባለሃብቶች ተሳትፈዋል፡፡

መድረኩ የኢትዮጵያን የኢንቨስትመንት አቅሞችና የተሻሻሉ የኢንቨስትመንት አስቻይ ሁኔታዎችን ለጃፓን ባለሃብቶች እንዲገነዘቡና በኢትዮጵያ መዋዕለ ንዋያቸውን እንዲያፈስሱ ለማበረታታት ነው ያለመ ነው ተብሏል።

አምባሳደር ዳባ ደበሌ÷ የሁለቱ ሀገራት ግንኙነት ረጅም ዘመናትን ያስቆጠረ እና በጋራ ጥቅም ላይ የተመሰረተ መሆኑን አውስተዋል፡፡

ኢትዮጵያ በተፈጥሮ ሃብት፣ በወጣት የሰው ኃይል፣ ሰፊ የገበያና በሌሎችም ሰፊ አቅም ያላት ሀገር መሆኗንና ኢኮኖሚውም በፈጣን ዕድገት ላይ የሚገኝ መሆኑን ጠቅሰዋል፡፡

በለጠ ሞላ (ዶ/ር ) በበኩላቸው÷ ኢትዮጵያ ለኢንቨስትመንት ምቹ መሆኗንና መንግስት ባካሄደው ኢኮኖሚ ማሻሻያ አስቻይ የኢንቨስትመንት ሁኔታዎች መፈጠራቸውን አውስተዋል፡፡

የጃፓን ባለሃብቶች እና ኩባንያዎችም በኢትዮጵያ ያለውን የኢንቨስትመንት ዕድል እንዲጠቀሙ ጥሪ አቅርበዋል፡፡

ባለሃብቶቹ በቀጣይ በኢትዮጰያ በተለያዩ የኢንቨስትመንት ዘርፎች ለመሰማራት ፍላጎት እንዳላቸው ገልፀዋል።

Exit mobile version