Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

የአምራቾችን ችግሮች ለመቅረፍ ያለመ ጉብኝት ተካሄደ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 21፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢንዱስትሪ ሚንስትር መላኩ አለበል እና የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ፕሬዚዳንት ዮሐንስ አያሌው (ዶ/ር) በገላን ከተማ የሚገኙ የስራ ዕድል በመፍጠር፣ የወጪ ንግድ ፍላጎት በማሟላትና ገቢ ምርትን በመተካት ላይ የሚገኙ አምራቾችን ጎበኙ፡፡

ከተጎበኙት መካከል÷ ኪት ፓኬጂንግ ማኑፋክቸሪንግ የካርቶንና የታሸጉ ወረቀቶች ማምረቻ እና ቢኬ የብረታ ብረት ኢንጂነሪንግ ኮምፕሌክስ የመኪና መገጣጠሚያ ይገኙበታል፡፡

የጉብኝቱ ዓላማ÷ ኪት ፓኬጂንግ ወደ ማምረት ሂደት እንዲገባ አስፈላጊውን ድጋፍ ለማድረግ እና በማምረት ሂደት ያለውን የፓኬጂንግ ድርጅት እያጋጠሙ ያሉ ችግሮችን መፍታት ነው፡፡

አቶ መላኩ አለበል ፋብሪካዎቹ ያሉበት ደረጃ አበረታች ነው ማለታቸውን የኢንዱስትሪ ሚኒስቴር መረጃ ያመላክታል፡፡

ፋብሪካዎቹ የገቢ ምርት በመተካት፣ ለዜጎች የስራ እድል በመፍጠር የውጭ ምንዛሬ ገቢ በማስገባት ትልቅ አስተዋጽኦ አላቸው ብለዋል፡፡

መንግስትም እያደረገ ያለውን ድጋፍ አጠናክሮ እንደሚቀጥል ጠቁመው÷ በቅንጅታዊ አሰራር መፈታት የሚገባቸው ችግሮችን ሚኒስቴሩ ከሌሎች ተቋማት ጋር በጋራ ለመፍታት እንደሚሰራ አረጋግጠዋል፡፡

ኪት ፓኬጂንግ ማኑፋክቸሪንግ የማሸጊያ ካርቶኖችና የማሸጊያ ወረቀቶች የሚያመርት ሲሆን÷ እንደ ሀገር ከውጪ የሚገባ የማሸጊያ ምርቶችን በአገር ውስጥ ለማስቀረት በሚደረገው ጥረት፣ የስራ እድል በመፍጠር እና በቀጣይም በኤክስፖርት ተሰማርቶ የውጪ ምንዛሬ ገቢን በማስገኘት ረገድ ሚና እንደሚኖረው ተገልጿል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
Exit mobile version