አዲስ አበባ፣ ሰኔ 21፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በኢትዮጵያ እና በቻይና መንግስታት መካከል የታዳሽ ኃይል የምርምር ማዕከል ለማቋቋምና የታዳሽ ኃይል አማራጭ ልማትን ለማስፋፋት ስምምነት ተደረገ፡፡
ስምምነቱ የተፈረመው÷ በውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር፣ በቻይና የግብርና ዩኒቨርሲቲ እና በወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ ነው፡፡
ፕሮጀክቱ በተባበሩት መንግስታት የልማት ፕሮግራም በኩል የሚተገበር መሆኑን የሚኒስቴሩ መረጃ ያመላክታል፡፡
በውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር የኢነርጂ ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ሡልጣን ወሊ (ዶ/ር ኢ/ር)÷ ስምምነቱ የታዳሽ ኃይል ማመንጨት ሂደትን የሚያግዝ የምርምር ማዕከል በማቋቋም የታዳሽ ኢነርጂ ግብዓቶችን ለማምረት የሚያስችሉ ሁኔታዎች በምርምር ለመደገፍ ያለመ ነው ብለዋል፡፡
በኢትዮጵያ የቻይና ኤምባሲ የኢኮኖሚና የንግድ ጉዳዮች አማካሪ ያንግ ይሃንግ በበኩላቸው÷ ኢትዮጵያ ያላትን የታዳሽ ኃይል ለሕዝቡ ጥቅም ላይ ለማዋል የምርምርና ኤክስቴንሽን ማዕከል መቋቋሙ ጉልህ ጠቀሜታ እንዳለው አስረድተዋል፡፡
የጋራ ምርምርና ኤክስቴንሽን ማዕከሉ የስልጠና እና የሰርቶ ማሳያ ማዕከል በመሆን የታዳሽ ኢነርጂ ቴክኖሎጂ ተደራሽነት አቅም ለማሳደግ ዘመናዊ የታዳሽ ኢነርጂ ቴክኖሎጂዎችን ከቻይና በማምጣት የእውቀት እና የቴክኖሎጂ ሽግግር ለማስተላለፍ ታሳቢ ያደረገ መሆኑን በሚኒስቴሩ የተባበሩት መንግሥታ ድርጅት የልማት ፕሮግራም ፕሮጀክት አስተባባሪ ሳህለ ተስፋዬ አስገንዝበዋል፡፡
#Ethiopia
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!