Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

በጋምቤላ ክልል ከ100 ሺህ በላይ ወጣቶች በበጎ ፈቃድ አገልግሎት ሊሰማሩ ነው

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 25፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በጋምቤላ ክልል ከ100 ሺህ በላይ ወጣቶችን በክረምት የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ለማሰማራት ዝግጅት መደረጉን የክልሉ ሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ አስታወቀ።

በአገልግሎቱ ከ270 ሺህ በላይ የክልሉን ህዝብ ተጠቃሚ ለማድረግ መታቀዱንም ቢሮው ገልጿል።

ጋምቤላ ከተማ አስተዳደርን ጨምሮ በክልሉ 14 ወረዳዎች ከ100 ሺህ የሚበልጡ ወጣቶች በክረምት የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ላይ እንደሚሰማሩና ለዚህም ዝግጅት መደረጉን የቢሮው ኃላፊ ክርሚስ ሌሮ ገልጸዋል፡፡

ወጣቶቹ ከሚሰማሩባቸው የስራ መስኮች መካከል የአረንጓዴ አሻራ፣ የአቅመ ደካማ ቤቶች እድሳት፣ የግብርና ልማትና የሰላም ግንባታ እንደሚገኙበትም ጠቅሰዋል።

እቅዱን ለማሳካትም በቅርቡ ወደ ክልሉ መጥቶ የነበረው ወሰን ተሻጋሪ የክረምት የወጣቶች በጎ ፈቃድ አገልግሎት ሰጪ ቡድንን በመጠቀም ከፍተኛ የንቅናቄና የማነሳሳት ስራዎች መከናወናቸውን አንስተዋል፡፡

በጋምቤላ ክልል ባለፈው ዓመት የክረምት ወቅት የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ከ60 ሺህ በላይ ወጣቶች ተሰማርተው የተለያዩ የልማት ሥራዎችን አከናውነዋል መባሉን ኢዜአ ዘግቧል ፡፡

Exit mobile version