አዲስ አበባ፣ ሰኔ 27፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) አገልግሎት አሰጣጡን ይበልጥ ለማዘመን ትኩረት ሰጥተን እየሰራን እንገኛለን ሲሉ የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤ ገለጹ፡፡
በ”ስማርት ሲቲ” እና ዲጂታል ትራንስፎርሜሽን ፅንሰ ሃሳብ ላይ ያተኮረ የግንዘቤ ማስጨበጫ ስልጠና ለባለድርሻ አካላት ተሰጥቷል፡፡
በግንዛቤ ማስጨበጫ መርሐ ግብሩ ላይ የተገኙት ከንቲባ አዳነች አቤቤ÷ ከተማዋን ለነዋሪዎቿ ምቹ እና አገልግሎት አሰጣጡን ዘመናዊ፣ ፈጣን እንዲሁም ዜጎች ያለምንም እንግልት አገልግሎት እንዲያገኙ እየተሰራ ነው ብለዋል፡፡
በተጨማሪ የቴክኖሎጂ ስራዎች በተደራጀ ሁኔታ የነዋሪውን ፍላጎት በሚያሟላ መልክ እንዲተዳደር በጥናት ተደግፎ አዲስ አደረጃጀት በመፍጠር ሥራዎችን እየሰራን እንገኛለንም ነው ያሉት፡፡
የከተማ አስተዳደሩ አገልግሎት አሰጣጡን በዲጂታል ቴክኖሎጂ ይበልጥ ለማዘመን ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ ነው ማለታቸውን የከንቲባ ጽህፈት ቤት መረጃ ያመላክታል፡፡
ተቋማት አዳዲስ ቴክኖሎጂዎችን ስራ ላይ በማዋል የህዝቡን እንግልት የሚቀንሱ አሰራሮችን መዘርጋታቸውንም ጠቁመዋል፡፡