Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

በመዲናዋ የ6ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና እየተሰጠ ነው

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 28፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በአዲሱ ሥርዓተ ትምህርት መሰረት የ6ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና እየተሰጠ ነው፡፡

ፈተናው በአዲሱ ሥርዓተ ትምህርት መሰረት ለመጀመሪያ ጊዜ በከተማ አስተዳደሩ በሚገኙ 182 የመፈተኛ ጣቢያዎች ነው እየተሰጠ የሚገኘው፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ዘላለም ሙላቱ (ዶ/ር) እና ሌሎች አመራሮች በየካ ክፍለ ከተማ በሚገኙ የመፈተኛ ጣቢያዎች ተዘዋውረው የፈተናውን አጀማመር ተመልክተዋል።

ፈተናው ያለምንም ችግር እንዲጠናቀቅ የጸጥታ አካላትን ጨምሮ ከተለያዩ ባለድርሻ አካላት ጋር በጋራ ሲሰራ መቆየቱንም ሃላፊው ተናግረዋል፡፡

በከተማ አስተዳደሩ ላለፉት ሁለት ቀናት የተካሄደው የ8ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ያለምንም እንከን መጠናቀቁንም አስታውሰዋል፡፡

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በ182 የፈተና ጣቢያዎች 75 ሺህ 90 ተማሪዎች የ6ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ለመውሰድ ተመዝግበዋል።

በአለምሰገድ አሳዬ

Exit mobile version