Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

ዶክተር ሊያ ታደሰ ከቻይና ጤና ቢሮ ልዑካን ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 28፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የጤና ሚኒስትር ዶክተር ሊያ ታደሰ ከቻይና ሀናን ግዛት ጤና ቢሮ ከመጡ የልዑካን ቡድን አባላት ጋር ተወያዩ፡፡

የጤና ሚኒስትሯ ÷ የጥሩነሽ ቤጂንግ ሆስፒታል  እንዲጠናከር አስፈላጊው ክትትልና ድጋፍ እየተደረገ መሆኑን በውይይታቸው ወቅት ገልጸዋል፡፡

ቻይና ያደረገችው ድጋፍ የሆስፒታሉን አገልግሎት ወደ ተሻለ ደረጃ ማሳደግ ያስችላልም ብለዋል፡፡

ሆስፒታሉ በድንገተኛና የአደጋ ሕክምና የላቀ አገልግሎት መሥጠት እንዲችል  እና በግብዓት እንዲጠናከር የቻይና መንግስት ድጋፍ እንዲያደርግ ጠይቀዋል፡፡

እስካሁን የቻይና ሕዝብና መንግሥት ላደረጉት ድጋፍም ምሥጋና ማቅረባቸውን የጤና ሚኒስቴር መረጃ ያመላክታል፡፡

Exit mobile version