አዲስ አበባ፣ ሰኔ 29፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የምስራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግስታት (ኢጋድ) ዋና ፀሐፊ ወርቅነህ ገበየሁ (ዶ/ር) እና የአፍሪካ ሕብረት ኮሚሽን ሊቀ መንበር ሙሳ ፋኪ ማህማት በሱዳን ወቅታዊ ጉዳይ ላይ መክረዋል።
ሁለቱ ተቋማት በሱዳን ሰላም እና መረጋጋት እንዲሰፍን ያላቸው ቁርጠኝነት የማይናወጥ መሆኑን ወርቅነህ ገበየሁ(ዶ/ር) በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው አስፍረዋል፡፡
ኢጋድ እና የአፍሪካ ህብረት በሱዳን ዘላቂ የሆነ የተኩስ አቁም ስምምነት እንዲደረስ፣ ጦርነቱ እንዲቆም እና ሀገሪቱን ወደ ፖለቲካው መስመር ለመመለስ በጋራ ጥረት እያደረጉ መሆኑንም አንስተዋል፡፡