አዲስ አበባ፣ ሰኔ 30፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በሰሜኑ ጦርነት ምክንያት ጉዳት ደርሶባቸው የነበሩ ሶስት ድልድዮች ተገቢው ጥገና ተደርጎላቸው አገልግሎት መስጠት መጀመራቸውን የኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር ገለጸ።
ጥገና የተደረገላቸው ድልድዮች ከመቀሌ ወደ ሐውዜን፣ ከአላማጣ ወደ መኾኒ እንዲሁም ከሰቆጣ ወደ ፃታ እና ማይጨው የሚወስዱ መንገዶች ላይ የሚገኙ ድልድዮች እንደሆኑ ተገልጿል።
በብረት ተሰርተው አገልግሎት መስጠት ከጀመሩ ድልድዮች መካከል ሁለቱ 36 ነጥብ6 ሜትር ርዝመት ያላቸው ሲሆን ከሰቆጣ ወደ ፃዳ እና ማይጨው የሚወስደው መንገድ ላይ የተጠገነው ድልድይ 48 ሜትር ርዝመት እንዳለው ተጠቁሟል።
ከዚህ ቀደም በአፋር፣ በአማራ እና በትግራይ ክልሎች ስድስት ድልድዮች ጥገና ተደርጎላቸው አገልግሎት መጀመራቸውን የኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር መረጃ አስታውሷል።