አዲስ አበባ፣ ሰኔ 30፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የአማራ ልማት ማኅበር (አልማ) በተጠናቀቀው በጀት ዓመት በአማራ ክልል 7 ሺህ 328 የመማሪያ ክፍሎች መገንባቱን ገለጸ፡፡
የማኅበሩ የሕዝብ ግንኙነትና ኮሙኒኬሽን ዳይሬክተር ዓለማየሁ ሞገስ ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት እንደገለጹት÷ በ2015 ዓ.ም በ1 ነጥብ 7 ቢሊየን ብር የመማሪያ ክፍሎች እና የጤና ተቋማት ተገንብተዋል፡፡
ማኅበሩ ከትምህረት ቤቶች በተጨማሪ ከ45 በላይ የጤና ተቋማት እና 46 ሼዶችን መገንባቱን ነው የተናገሩት፡፡
አልማ ከአባላቱ በሚሰበስበው ገንዘብ በክልሉ ለሚገኙ ትምህርት ቤቶች የመማሪያ ክፍሎችን ጥገና እና አዳዲስ ክፍሎችን በመገንባት በየደረጃው ላሉ የትምህርት ተቋማት አስረክቧል ብለዋል፡፡
በክልሉ የትምህርት ተቋማት አብዛኛዎቹ ከደረጃ በታች መሆናቸውን ጠቅሰው÷ የልማት ማኅበሩ በትምህርት ተቋማት ግንባታ ላይ በትኩረት እየሠራ መሆኑን አስገንዝበዋል፡፡
በጳውሎስ አየለ