Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

የፖርቹጋል ባለሃብቶች በኢንዱስትሪ ፓርኮችና በድሬዳዋ ነፃ ንግድ ቀጠና መዋዕለ ንዋያቸውን እንዲያፈሱ ተጠየቀ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 30፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የፖርቹጋል ባለሃብቶች በኢንዱስትሪ ፓርኮችና በድሬዳዋ ነፃ ንግድ ቀጠና በዘርፈ ብዙ የኢንቨስትመንት አማራጮች እንዲሰማሩ የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ጥሪ አቅርቧል፡፡

የኮርፖሬሽኑ ዋና ስራ አስፈፃሚ አክሊሉ ታደሰና ልዑካቸው በኢትዮጵያ ከፖርቹጋል አምባሳደር ሉዊዛ ፍራጎሶ ጋር ውይይት ተወያይተዋል፡፡

በውይይታቸውም ኢትዮጵያና ፖርቹጋል በኢንቨስትመንት፣ በኢኮኖሚ እና በሌሎች የትብብር መስኮች ያላቸውን ግንኙነት አጠናክረው መቀጠል በሚችሉባቸው ጉዳዮች ላይ ሀሳብ ተለዋውጠዋል።

ባለሀብቶች በኢንዱስትሪ ፓርኮችና በድሬዳዋ ነፃ ንግድ ቀጠና በዘርፈ ብዙ የኢንቨስትመንት አማራጮች እንዲሰማሩ ዋና ስራ አስፈጻሚው ጥሪ ማቅረባቸውን ከኮርፖሬሽኑ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

በቀጣይም ሁለቱ ሀገራት በተለይም የኢንቨስትመንት ግንኙተታቸው ተጠናክሮ እንዲቀጥልና የፖርቹጋል ባለሃብቶች ወደ ኢትዮጵያ በመምጣት ኮርፖሬሽኑ በሚያስተዳድራቸው ኢንዱስትሪ ፓርኮችና ድሬዳዋ ነፃ ንግድ ቀጠና በዘርፈ ብዙ ኢንቨስትመንቶች እንዲሰማሩ ለማድረግ ስራዎች እንዲሰሩ ከመግባባት ላይ ደርሰዋል።

Exit mobile version