አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 30 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ)በርካታ የተሰረቁ ላፕቶፖችና የኮምፒውተር እቃዎች ከ4 ተጠርጣሪዎች ጋር በቁጥጥር ስር መዋላቸውን የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታወቀ።
ተጠርጣሪዎቹ በቁጥጥር ስር የዋሉት በአዲስ አበባ ከተማ በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ወረዳ 8 በ3 የኮምፒውተር ጥገና ሱቆች ውስጥ ነው።
ግለሰቦቹ ህጋዊ የንግድ ፍቃድን ሽፋን በማድረግ ከተለያዩ አካባቢዎች የተሰረቁ ላፕቶችንና ኮምፒውተሮችን እየተቀበሉ በርካሽ ዋጋ እንደሚሸጡ በተደረገ ክትትል መረጋገጡን ከአዲስ አበባ ፖሊስ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
በዚህም በ3 የኮምፒውተር ጥገና ሱቆች ውስጥ በተደረገ ብርበራ 31 ላፕቶፖች፣ 42 ሞኒተር፣14 ኪቦርድ እና 1 ታፕሌትን ከ4 ተጠርጣሪዎች ጋር በቁጥጥር ስር ውለው ምርመራ እየተጣራ መሆኑ ተገልጿል፡፡